በደቡብ አፍሪካ አርበኞች ግንቦት7 ከፍተኛ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ መስራቱን አስተባባሪዎች ገለጹ

ጥቅምት ፲ (አሥር) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአገሪቱ የንቅናቄው ተወካዮች እንደገለጹት በተከታታይ ቀናት በተደረገው የገቢ ማሰባሰብ ስራ በደርባን 236 ሺ 400 ፣ በጆሃንስበርግ 252 ሺ ፣ በፕሪቶሪያ 180 ሺ፣ እንዲሁም በራስተምበርግ110 ሺ በአጠቃላይ በአራቱ ከተሞች በጨረታ ብቻ 778 ሺ 400 ራንድ ወይም  1 ሚሊዮን 334 ሺ 400 የኢትዮጵያ ብር አሰባስበዋል።

በሁሉም ከተሞች በተደረገው የገቢ ማሰባሰብ ስራ የህዝቡ የትግል ስሜትና ድጋፍ የሚገርም ነበር ያሉት አስተባባሪዎች፣ በሁሉም ስብሰባዎች ላይ የኦሮሞ ማህበረሰብ እና  የሶማሊ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተው በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ መልእክት አስተላልፈዋል። “የአማራ ደም የኦሮሞ ደም ነው፣ የኦሮሞ ደም የአማራ ደም ነው” የሚል መልእክት በሁሉም ቦታዎች ላይ ይተላለፍ እንደነበርም ገልጸዋል።