በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ጦርነት እንደገና አገረሸ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ውጤት አለማምጣቱን የሚያሳይ ጦርነት በነዳጅ ሃብቷ በበለጸገቸው የቤንቲዩ ግዛት መጀመሩን ዘገባዎች የመለክታሉ።

በሪክ ማቻር የሚመራው የአማጽያኑ ሃይል ቤንቲዩን መቆጣጠሩን ሲያስታውቅ፣ የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር መንግስት ደግሞ ዜናውን አስተባብሎአል።

እንደገና ባገረሸው ጦርነት አመጽያኑ ድል እንዳገኙና በመሸሽ ላይ ያሉትን የመንግስት ወታደሮች እየተከታተሉ በመውጋት ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞቹ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፤ ግጭቱ በአፋጣኝ ካልቆመ ለምስራቅ አፍሪካ ሊተርፍ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

በርካታ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ እየገቡ ነው፡፤