ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ደጋፊዎች ሳይሆኑ አይቀርም የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መጠለያ ግቢ ውስጥ በሰነዘሩት ጥቃት ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዚህ በሁዋላ ጥቃት ቢፈጸም አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
በአገሪቱ የሚታየው ጦርነት ወደ ጎሳ ግጭት ያመራል ተብሎ እየተፈራ ነው። ፕ/ት ሳልቫኪር በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ የሰላም አስከባሪ ሃይል ወደአገራቸው እንዲላክ እየጠቁ ነው።