ነሃሴ ፪(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አካባቢው በከፍተኛ አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ አርፍዷዋል፡፡በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል። የደሴ ህዝብ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማወቅ በፊድራል ፖሊስ ሐይሎች ሆስፒታሎች በመከበቡ ለማወቅ አልተቻለም።
በደሴ የሚኖሩ ሙስሊሞች 2 ሰዎች መገደላቸውን ለኢሳት ተናግረዋል
በአማራ ክልል በወረባቡ ከተማ ፤ እና መርሳ አካባቢ ክፍተኛ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን በሙስሊሙ እና በፖሊሶች መካከል በስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ዘጠኝ ምእመናን ታስረዋል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ በከተማዋ ላይ ተክቢራ ማሰማት ከልክለዋል፡፡