ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በከተማዋ የሚኖሩ ሙስሊሞች በዋናው መስጊድ ግቢ በመገኘት መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም፣ መጅሊሱ ወይም የእስልምና ጉባኤው ሙስሊሙን የማይወክል በመሆኑ እንዲፈርስ እንዲሁም የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል።
የመንግስት ባላስልጣናት ሙስሊሞቹ ተወካዮቻቸውን መርጠው እንዲነጋገሩ ባሳሰቡት መሰረት 50 ተወካዮች ከሰአት በሁዋላ የዜን የጸጥታ ሀላፊ፣ የዞን አስተዳዳሪ፣ የደሴ ከተማ እና ሌሎችም 9 ባለስልጣኖች ባሉበት ውይይት ተካሂዷል።
የዞኑ ባለስልጣናት ጉዳዩን ከክልል ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረው እስከ ጥር 30 ድረስ መልስ እንደሚሰጡ ለተወካዮች ገልጸዋል። እስከዚያው ድረስ ግን የአህባሽ አስተምህሮ እንቅስቃሴ እንዲቆም አዘዋል።
በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ሙስሊሞች ፣ የእምነት ነጻነት እንዲከበርላቸው ጥያቄ እያነሱ ነው።
በቅርቡ በአወልያ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ኮሌጅ ተመሳሳይ ተቃውሞ መደረጉ ይታወሳል።
በደቡብ ወሎ ዞን፣ በቃሉ ወረዳ በስቲማ እና ደጋን ከተሞች ተመሳሳይ ተቃውሞ ተከስቶ ነበር።
የሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት መሪዎቹን ራሱ እንዲመርጥ፣ መንግስት አህባሽን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ሩጫ እንዲያቆም፣ የእስልምና ጉባኤ መሪዎች በመንግስት እንጅ በሙስሊሙ ያልተመረጡ በመሆኑ እንዲወርዱና አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ይጠይቃሉ።