በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ

በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ
(ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በደሴ ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ የታክሲና የአውቶቡስ መጓጓዣ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።መረጃዎች እንዳሳዩት፣ በተለይ በከተማዋ የታክሲ ዋጋ ላይ ሃምሳ በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ‘’በዓለም ላይ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ባለበትና ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር ለምን የዋጋ ጭማሪው ማድረግ አስፈለገ?’’ ሲሉ ነዋሪዎቹ ቢጠይቁም፣ ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ግን አላገኙም። ከመጓጓዣ ጭማሪው በተጓዳኝም የዋጋ ንረቱን መቋቋም እንዳልቻሉም ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ደሴ ላይ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ2 ሽህ 300 ጀምሮ ይሸጣል። “አንድ ሁለት ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ የሚያገኝ አባወራና ጤፍ አይተዋወቁም።‘’
በመላው አገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በፈጠረው የኑሮ ውድነት ምክንያት ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ እየተማረሩ ነው። ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መደረጉም የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ አባብሶታል።