በኬንያ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ታሰሩ

ሰኔ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በላሙ የወደብ ዳርቻ ሰሞኑን የተፈጸመው ጥቃት የ60 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጥቃቱን የፈጸመው አልሸባብ አለመሆኑን ገልጸው ነበር። ጥቃቱ በአልሸባብ እንደተፈጸመ ተደርጎ መረጃውን ያሰራጨውን ሰው መያዙም ተገልጿል።

ግድያው ከጎሳ ፖለቲካ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአገሪቱ መንግስት ገልጿል። ሰሞኑን በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 12 ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል። ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንደገቡ የታወቀ ነገር የለም።

ኬንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ሃይሎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባት ነው።