(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010) በደቡብ ኢትዮጵያ ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ለውጡን እንደግፍ በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ።
በኢትዮጵያ ሰንድቅ ዓላማ ያሸበረቀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የቦንጋና አከባቢዋ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ከባህርዳር ቀጥሎ ረጅም የተባለው ሰንደቅ ዓላማ በሰልፉ ላይ መታየቱንም ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል በአርባምንጭ ኢትዮጵያዊነትን እናክብር በሚል መሪ ቃል ለውጡን ለመደግፍ የታቀደውን ሰልፍ የጸጥታ አካላት እያደናቀፉት ነው ሲሉ አዘጋጆቹ ገለጹ።
የቅስቀሳውን ዝግጅት በማስተጓጎል ሰልፍ እንዳይካሄድ የወከባ ተግባር በጸጥታ ሃይሎች እየተፈጸመ ነው ሲሉም ተናግረዋል።