በኩዌት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን አንቃ መግደሏን አመነች

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኩዌት ሃዋሊ በተባለዉ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን በገመድ አንቃ እንደገደለች ማመኗን አረብ ታይምስ የመረጃ ምንጭ ገልጧል

“የቤት ሰራተኛ እራሷን በገመድ ሰቅላ አጥፍታለች “ በማለት ማንነቱ ካልታወቀ ሰዉ በደረሳቸዉ ጥሪ መሰረት የፀጥታ ሰራተኞችና አስቸኳይ የህክምና ቡድን /ፓራሜዲክስ/ በስፍራዉ ተገኝተዋል።

ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራዎች በሚደረጉበት ወቅት ሟች እራሷን እንዳልገደለችና ለምን እንደሆነ ምክንያቱን ያልገለፀች ኢትዮጵያዊ ወገንዋ አንቃ የገደለቻት መሆኗን አምናለች። ጉዳዩ በመጣራት ላይ አረብ ታይምስ ገልጿል።

በሌላ በኩል አል-ዋታን የተባለዉ እለታዊ የአረብኛ ጋዜጣ እንደገለፀዉ አንዲት በኩዌት ነዋሪ የሆነች ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ በስፖንሰሯ ወንድ ልጅ ክፉኛ ተደብድባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል። ልብሶቹ በፍጥነት ስላልተተኮሱለት በተሰማዉ ንዴት ባደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ ያሰማችዉን የድረሱልኝ ርዳታ ጥሪ የሰሙ መንገደኞች በአቅራቢያዉ ለሚገኘዉ የፋራ-ዋኒያ የፖሊስ ጣቢያ ባደረጉት ጥሪ ህይወቷ መትረፉን ለማወቅ ተችሏል። ፖሊስ ወንጀለኛዉን ለጥያቄ እንደሚጠራዉ መግለፁን የዜና ምንቹ ገልጿል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide