ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆችና አቃቢ ህግ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ተንተርሶ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣
15ኛወንጀልችሎትበነመላኩፈንታየክስመዝገቦችክስመቃወሚያላይለዛሬብይን ለመስጠት ይዞትየነበረውን የመጨረሻ ቀጠሮዳግምያራዘመው የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት መንገድ ዳር በመሆኑ በስፍራው ያለው ድምጽ ችሎቱን ለመሰየም አያስችልም በሚል ምክንያት ነው።
ችሎቱ በፊት ሲደረግ እንደነበረው በልደታ ፍርድ ቤት ግንቦት22፣ 2006 ዓም እንዲካሄድ ሲወስን ጠበቆች ግን ፍርድ ቤቱ ችሎቱን ወደ ቃሊቲ ሲያዞር አስቀድሞ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነበረበት በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል። ዳኞች በበኩላቸው ከቀጣዩ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት ችግር አይፈጠርም ብለዋል።
ችሎቶችን በሰበብ አስባቡ ማራዘም እና እስረኞችን ማጉላላት በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተለመደ ነገር ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮምፒዩተር የለንም፣ ዳኛ አልተሟላም፣ ብይን አልደረሰለንም በሚሉ ሰበብ አስባቦች ችሎተ የማራዘሙ ሂደት እየጨመረ መምጣቱን ዘገቢያችን አስተያየቱን አሰፍሯል።