(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጸሙት ወንጀል በሃገራቸው ፍርድ ተላለፈባቸው።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2014 እስከ 2017 በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩት ኪምኩን ሁዋን ከትላንት በስቲያ ረቡዕ የአንድ አመት እስራት የተፈረደባቸው በወሲባዊ ትንኮሳና ድርጊት ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው።
በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር በነበሩት ወቅት ከእርዳታ ሰጪ ድርጅት ሰራተኛና ከኤምባሲው ሰራተኛ ጋር ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸም የተወነጀሉት ኪም ሙን ሁዋን ከእስራቱ በተጨማሪ፣የ40 ሰአታት ህክምናም ታዞላቸዋል።
ሕክምናው ከወሲባዊ ትንኮሳ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሚያደርግ ሲሆን እስራታቸው ሰጨርሱም ከወጣቶችና ሕጻናት ጋር በተያያዙ ተቋማት ውስጥ እንዳይሰሩም ታግደዋል።
በባህር ማዶ የሐገሩ ዜጋ ዋና ተሟጋችና ጠባቂ ሃላፊነት ተሰጥቶት ሃገሩን በበጎ ማስነሳትና የዜጎችንም ደህንነት ማስጠበቅ ሲገባው ሃላፊነቱን ለእኩይ ድርጊት አውሎታል ያለው ሲኦል ላይ ያስቻለው የማዕከላዊ ፍርድ ቤት ረቡዕ ዕለት የአንድ አመቱን እስራት ፈርዶ ወድ ወህኒ ልኳቸዋል።
አምባሳደሩ በሁለት ሴቶች ላይ ፈጸሙ የተባለውን የወሲብ ትንኮሳ ያስተባበለ ሲሆን ሰስተኛውን በስምምነት የተፈጸመ ነው በማለት የቀረበባቸውን ክስ ተከላክለው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን ውድቅ አድርጎታል።