መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ስብሰባ ተከትሎ በአዋሳ፣ አዳማ እና ባህርዳር ጥብቅ ፍተሻ መካሄዱን የአይን እማኞች ገለጹ
በተለይ በአዳማ እና በአዋሳ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ፍተሻ ከቅዳሜ ከሰአት ጀምሮ እስከ ዛሬ መካሄዱ ታውቋል። ወደ አዋሳ ከተማ የሚገቡ ሰዎች በጥብቅ የተፈተሹ ሲሆን፣ በከተማዋ ውስጥም በአንዳንድ ቦታዎችም ፍተሻዎች ተደርገዋል። በአዋሳ የተለያዩ ቦታዎች ድንኳኖች ተተክለው የኢህአዴግ ደጋፊዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲጨፍሩ የታዩ ሲሆን፣ ከ30 እሰከ አርባ የሚደርሱ ሰዎች በድንኳኖች ዙሪያ ይታዩ ነበር። በአዳማ ደግሞ ኢህዴድን እንዲደግፉ የተጠሩ ሰዎች ሳይቀር ጥብቅ ፍተሻ ተደርጎባቸዋል። ጥሪ የተደረገላቸው የቀበሌ ሰዎች ባለመገኘታቸው የኦህዴድ ካድሬዎች በእጅጉ መበሳጨታቸውን ከአባለቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
በትግራይ መቀሌ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ደግሞ የህወሀት ኩባንያ ንብረት የሆነው ኢፈርት መኪኖች ሰልፉን አድምቀውት ውለዋል።
ነዋሪዎች የሰልፉ አላማ ግራ ሲያጋባቸው ታይቷል። ኢህአዴግ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ህዝቡ እንዲደግፈው ጥሪ ማቅረቡ ድርጅቱ የገባበትን የውስጥ ፍርሀት የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ አባላት ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል።
ኢህአዴግ በውስጥ የተፈጠረውን ሽኩቻ በመጪው ጉባኤ እንዲፈታ የስርአቱ ደጋፊዎች እየተማጸኑ ነው።
አሁን በደረሰን ዜና ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ነዳጅ ማደያ ቦታዎች በሙሉ በል ዩ ት ዛ ዝ ካልሆነ በስተቀር ለማ ንም ነዳጅ እንዳይሸጡ ታዘዙ!!! በዚህም ምክንያት በከተማው ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ ከፍተኝ የሆነ የ ትራንስፖርት እጥረት ተከስቱዋል ትቂት ባጃጆች በስራ ላይ ያሉ ሲሆን በሊትር ሃያ ብር የሚሸተወን ቤንዚን በሃያ አምስት ብር ከ አትራፊ ቸርቻሪዎች ለመግዛት ተገደዋል።ነዳጅ እያለ እንዳይሸጥ የተደረገበት ምክንያት ሰሞኑን እየተካሄደ ባለው የመንግስት ስብሰብባ ምክንያት ነው ተብ ሉዋል።