ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች።
ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በወለደች በማግስቱ ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።
ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው።
ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ነው።
ጓደኛዋም ከጋብቻ ውጪ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ወንጀል ተከሶ በ እስር እንደሚገኝ< አመልክቷል።
የ አንድ ቀን አራሷ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ሁለት እግሮቿ በሰንሰለት በመታሰራቸው፤ ህፃን ልጇን ሜሪያምን ማቀፍ ተስኗት መታየቷን ድረ-ገጹ አስነብቧል።
ኢትዮጵያዊቷ እናት ለፍርድ ቤት በሰጠችው ቃልም ከእስር ከተለቀቀች ከህፃኗ ጋር ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ተናግሯለች።
የወህኒዎቹ ሃላፊዎች ግን አራሷ ኢትዮጵያዊት ከወህኒ የምትወጣው የ እስር ጊዜዋን ከጨረሰች በሁዋላ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ህፃን ልጇን ይዛ መሄድ ትችላለች?ወይስ አትችልም? የሚለው ጉዳይም ለወደፊት በ ህግ የሚታይ መሆኑን ነው የገለፁት።
ወደ መካከለኛው ምስራቅና አረብ አገራት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ደረጃ በደረሰበት ሰ ዓት የ ኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመታደግ ምንም እንቅስቃሴ ሲያደርግ አመታዬቱ፤ ብዙዎችን ካሳዘነ ውሎ አድሯል።