በአፋር ገዋኔ የህዝብ ቁጣን ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 26/2011) በአፋር ገዋኔ በመከላከያ የተገደለው ወጣት ጉዳይ የህዝብ ቁጣን መቀስቀሱ ተሰማ።

ሰልፈኞቹ የመከላከያ ሃይሉ ከገዋኔ ይውጣልን፣ገዳዮች ለህግ ይቅረቡልን፣ኮንትሮባንዲስቶች በህግ ይጠየቁልን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ማሰማታቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

የአፋር ወጣቶች ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ አመራር በሶስት ወራት ውስጥ እንዲሰራ የተቀመጠለትን የቤት ስራ አልሰራም በሚል በተለያዩ ወረዳዎች ህዝባዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ በክልሉ ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ለኢሳት ተናግረዋል።