በአዲ ዳዕሮ ህዝቡ ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት በሚከሰቱ ከአድዋ ውሃ በቦቲ እየተወሰደ እንዲከፋፈል ተደርጓል። የከተማዋ ነዋሪዎች በቦቴ ከሚመጣው ውሃ ለመቅዳት ረጃጀም ወረፋዎችን መጠበቅ ግድ ብሏቸዋል። ከአድዋ የሚጫነውም ውሃ አልፎ አልፎ እንጅ በየጊዜው እንደማይመጣ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
በተመሳሳይ ዜና በሃድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውሃ ከተቋረጠ ከሳምንት በላይ መሆኑንና ህዝቡ ለከፍተኛ ችግር መዳረጉን የአካባቢው ምንጮች ጠቅሰዋል።