በአዲስ አበባ የሚታየው የመጓጓዣ ችግር እንደቀጠለ ነው

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በከተማው ውስጥ በሚታየው የትራንስፖርት ችግር ተማሪዎችም ሆነ የመንግስት ሰራተኞች በሰአቱ ትምህርትቤታቸውና  ስራ ቦታቸው ለመገኘት አልቻሉም። በተለይ ከጧቱ 1 ሰዓት ተኩል እስከ 2 ሰዓት ተኩል እንዲሁም ከ ሰአት በሁዋላ ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በአራት ኪሎ፣ ሜክሲኮ፣ ሀያሑለት፣ ፒያሳ፣ መርካቶና ቦሌ አካባቢዎች ከፍተኛ  የሆነ የትራንሰፖርት ችግር ይከሰታል።

በቅርቡ ግንባታው የሚጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋት ችግሩን ይቀርፋል ብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።