ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማደስና ፕላን ዝግጅት በሚባለው ፕሮግራሙ በመሃል አዲስ አበባ የሚገኙ ኪስ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በስፋት እንደሚያፈናቅል የሚነገርለትን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
አካባቢን መልሶ የማልማት ገጽታ አለው በሚባለው ሥራ ውስጥ ዘንድሮ ከተካተቱ አካባቢዎች መካከል በካዛንቺስ 26 ሄክታር፣በደጃችውቤ 11.6 ሄክታር፤በሸበሌሆቴልዙሪያ 10.4 ሄክታር፣አሜሪካንግቢ 16 ሄክታር፣በአፍሪካህብረትቁጥር 2 ወደ 15 ሄክታር፣ተክለሃይማኖት 33 ሄክታር፣አሮጌውቄራቁጥር 1 እና 2እንደቅደምተከተሉ 14 ሄክታርእና 54 ሄክታር፣ባሻወልዴቁጥርየፓርላማማስፋፊያ 4 ሄክታርቤት የማፍረስ እቅድ መኖሩን ተከትሎበአንዳንድአካባቢዎችለነዋሪዎችካሳየመክፈል፣በአንዳንዶቹምየማፍረስሥራዎችእየተከናወኑመሆኑን ምንጮቹጠቅሰዋል፡፡
አስተዳደሩበመልሶማልማትፕሮግራሙበተለይየቀበሌቤቶችውስጥየሚኖሩነዋሪዎችምትክየኮንዶምኒየምቤትየሚሰጥቢሆንምበወቅቱናበሰዓቱየሚከናወንባለመሆኑነዋሪዎችለእንግልትናለተጨማሪወጪእየተዳረጉነው፡፡
በተለይየግልቤቶችምትክቦታበተመሳሳይሁኔታበፍጥነትየሚከናወንአለመሆኑ፣በቂየዝግጅትጊዜሳይሰጥነዋሪዎችእንዲነሱመገደዳቸውበየአካባቢውያላቸውንማህበራዊትስስርየሚያናጋናልጆቻቸውንምትምህርታቸውንለማስቀጠልየሚቸገሩበትሁኔታተፈጥሮአል፡፡በተለይበግለሰብቤቶችተከራይተውየሚኖሩበርካታነዋሪዎችበምትክቤቶችአሰጣጥውስጥየማይካተቱመሆኑማህበራዊቀውስእየፈጠረእንደሚገኝታውቋል፡፡
የከተማአስተዳደሩበተለይበሊዝጨረታቦታዎችንአወዳድሮሲሰጥየመሬትአቅርቦቱእጅግአነስተኛከመሆኑጋርተያይዞበአንድካሬሜትር 10ሺብርእናከዚያበላይየሚሰጡጥቂትሐብታሞችተጠቃሚየሚሆኑበት፣በአንጻሩአነስተኛናመካከለኛገቢዎችያላቸውነዋሪዎችየማይጠየቁበትሥርዓትመፈጠሩይታወቃል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት እጅግ በውድ ዋጋ የሚሸጠው መሬት በሙስና እየተበላ መሆኑንም የሚደረሱት መረጃዎች ያመለከታሉ። የኢሳት ምንጮች እንደሚገልጹት ከመሬትና ከታክስ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የዝሪፊያ መረብ የተዘረጋ ሲሆን፣ ምርጭ የሚባሉ ቦታዎች በእነዚህ ጥቂት ግልሰቦች እጅ እየገባ ነው።
እነዚህ ሰዎች ገቢዎችንና ጉሙሩክን ከጀርባ ሆነው በመቆ|ጣጠርና ስራቸውን በንጽህናና በሃቀኝነት የሚሰሩ ሰራተኞችን በተለያዩ ወንጀሎች በመክሰስ ከስራ እንዲባረሩ በማድረግ ከፍተኛ ሃብት እየመዘበሩ መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ታክስ ማጭበርበርና መሬት በህገወጥ መንገድ መዝረፍ በኢትዮጵያ አቋራጭ የመክበሪያ ስልት እየሆነ ነው።