የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-እነዚህ ቤቶች የተለያዩ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችንና ፊልሞችን እንደሚያሳዩም በግልፅ በፃፏቸው የውስጥ ግርግዳ ማሳታወቂያዎቻቸው ላይ ለጥፈዋል።
የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና እንደገለጠው በ 4 ኪሎ፤22፤ካሳንቺስ፤6 ኪሎና አውቶቡስ ተራ እንዲሁም ሳሪስ አካባቢዎች የሚገኙ ቤቶች የወንጀል መስሪያ ቦታዎች ሆነዋል።
አንዳንዶቹ የኳስ ማሳያ ቤቶች ከበስተጀርባቸው የጫት መቃሚያና የሺሻ ማጨሻ ሆነዋል ያሉት የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱሰትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ታየ ጫላ ሲሆኑ፣ በመርካቶ 7ኛ አካባቢ ባሉት ቪዲዮ ቤቶች ደግሞ ከባህል ውጭ የሆኑ የወሲብ ፊልሞች በግልጽ ይታይባቸዋል።
በከተማው የትኛውም ቦታ ባሉ አብዛኛው ቪዲዮ ቤቶች ፊልሞቹም እስፔሻልና ኖርማል ተብለው ተከፍለዋል። እስፔሻል የወሲብ ሲሆን ኖርማል ደግሞ ሌሎች ፊልሞች ናቸው፣ ወጣቶችም ለእስፔቫል 2 ብርና ለሌላ ፊልም ደግሞ 1 ብር ከፍተለው ይወለከታሉ ይላሉ።
ከ13 አመት ጀምሮ ያሉ ታደጊ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ወደ እነዚህ የወሲብ ፊልም ቤቶች ይሄዳሉ። ከቪዲዮ ቤቶቹ አጠገብ ደግሞ በወሲብ ስራ የሚተዳደሩ በትንንሽ ቤቶች ውስጥ ቆመው ደንበኞቻቸውን የሚጠብቁ ሴቶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መበራከቱ ተገልጧል።
የፊልም ቤቶች እና የሴተኛ አዳሪዎች መበራከት ከአገሪቱ አጠቃላይ ችግር ጋር የሚታይ መሆኑን የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች ይናገራሉ። መንግስት በአሁኑ ጊዜ ለወጣቶቹ የስራ እድል ለመፍጠርና በቂ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማዘጋጀት ባለመቻሉ፣ ወጣቶቹ ከባህላቸው ውጭ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችን ሲመለከቱና ለበሽታ ሲዳረጉ እርምጃ አይቶ እንዳላየ ያልፈዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች የኑሮ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ መልክ እየያዘ መምጣቱም ይነገራል።
ወጣቶቹ ስራ ለመያዝ የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ መጠየቃቸው፣ ተምረው ስራ ለማግኘት የሚገጥማቸው ፈተና ጊዜያቸውን አላስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች እንዲያሳልፉ እንደሚያደርጋቸው ጥናቶች ያሳያሉ።