መስከረም ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት ከቀኑ 4 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ በአዲስ አበባ መርካቶ በአንድ ሚኒባስ ታክሲ ላይ ተጠምዷል በተባለ ፈንጂ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር።
ረፋዱ ላይ ወደ አውቶቡስ ተራ አምባሰል ሙዚቃ ቤት አካባቢ የደረሰው ሚኒባስ ታክሲ በውስጡ ፈንጂ ተጠምዶበታል በመባሉ ከውስጡ ተሳፋሪ የነበሩ ሰዎች በትርምስ ሲወርዱ እና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሲሸሹ ከፍተኛ ትርምስ የተፈጠረ ሲሆን ፣ ብፍጥነት ወደ ታክሲው የመጡት የፌደራል ፖሊስ ልዩ አባላት ሰዎች ከአካባቢው በመራቅ እና ሱቆች እንዲዘጉ አድርገው ወደ ታክሲው ቀርበዋል ሲሉ የአይን እማኞች ለዘጋቢያችን ገልጠዋል።
በስፍራው የደረሰው ዘጋቢያችን እንዳስተዋለው ሚኒባሱ አምባሰል ሙዚቃ ቤት አካባቢ ቆማ መመልከቱን ፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን ከበው ሰው እንዳይተላለፍ ወደ አምዴ መዞሪያ፣ አውቶቡስ ተራ መገንጠያ ፣የሰባተኛ መንገድ እና በተለምዶ ፋሲል መድሀኒት ቤት የሚባለው አካባቢ በመዝጋት ሰዎችን እና መኪናዎችን እንዳያንቀሳቅሱ ከልክለው ቆይተዋል።
ዘጋቢያችን የአቃቢውን ሰዎች ሁኔታ እንዳስተዋለሁ የተወሰነ የመደናገጥ እና ምን እየተካሄደ እንዳለ ለመመልከት የመጓጓት ስሜት ይታይባቸው የነበር
አንዳንድ ሰዎች አሸባሪዎች ታክሲው ላይ አጥምደው ወርደው ነው የሚሉ ሀሳቦችን የሰነዘሩ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ኢህአዴግ
ኢህአዴግ እንደለመደው በራሱ ጊዜ ፈንጅ በማጥመድ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ነው በማለት ተናግረዋል።
ከግማሽ ሰአት በሁዋላ ሁኔታው ሊረጋጋ መቻሉን ዘጋቢያችን ገልጧል። የኢህአዴግ መንግስት በአዲስ አበባ ፈንጆችን በማጥመድ ፍንዳታ ያደርስ እንደነበር የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት በመጥቀስ ዊኪሊክስ መዘገቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።