መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምዘና ፈተና ጋር በተያያዘ በተማሪዎችና እና በዩኒቨርስቲው አስተዳደር መካከል በተፈጠረ ልዩነት ከ3 ሺ በላይ ተማሪዎች ዩኒቭረስቲውን ለቀው እንዲወጡ በመታዘዛቸው በቤተክርስቲያናትና በሰዎች ቤት ተጠልለለው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ ከእረፍት በተመለሱበት ማግስት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ የምዘና ፈተና ውሰዱ መባላቸውን ተቃውመው ተጨማሪ የጥናት ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ችግር መፈጥሩን ገልጸዋል።
የዩኒቨርስቲው ዲን በተማሪዎችላይ የተለያዩ ታፔላዎችን እየለጠፉባቸው መሆኑን የሚናገሩት ተማሪዎች፣ ዲኑ ምግብ ከመከልከል በተጨማሪ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እንዳስደረጉዋቸው ተናግረዋል።
ለከፍተና ችግር መጋለጣቸውን የተናገሩት ተማሪዎች ህብረተሰቡ እንዲታደጋቸውም ተማጽነዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።