በአማሮ ወረዳና በጉጂ መሃል ያለው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ታሰማ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) አንድ አመት ያስቆጠረዉ ግጭት ሰሞኑን ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በዳኖ፤ ደርባ እና ቲፋቴ ግጭቱ ተባብሶ የሰዎች ህይወት አልፏል። ዳኖ በሚባል ቀበሌ ከብቱን በመጠበቅ ላይ የነበረ ደመቀ ደባሱ የሚባል የ44 ዓመት ጎልማሳ አርሶአደር ወዲያውኑ ሲገደል፣ በቲፋቴና ደርባ ቀበሌዎች ደግሞ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት እኩለ ቀን ጊዜ ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ልዉዉወጥ ሲደረግ ቆይቷል። በተኩሱ ምክንያት የቆሰሉና የሞቱትን ሰዎች በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ በርካታ ሰዎች እንደተጎዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በዳኖ ቀበሌ የደረሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ11 የአማሮ አርሶ አደሮች መሳሪያ ማስፈታታቸዉ ተከትሎ፣ መሳሪያ መፍታት ያለባቸዉ ሁለቱም ወገኖች ናቸው በሚል በአማሮ ወረዳ ህዝብ ቅሬታ መፈጠሩን ናሪዎች ተናግረዋል።
ከአማሮ ዲላ የሚወስድ መንገድ ለ 3 ተከታታይ ወራት ዝግ መሆኑ ዜጎችን ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። ከቡሌ ሆራና ከወረዳዉ ቆላማ ቀበሌዎች በተለይ ከዶርባዴና ጀሎ የተፈናቀሉ ከ 21 ሺ በላይ ዜጎችም እገዛ በማጣት ለ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ።