ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን የጽ/ቤት ሃላፊና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቁጫቸውን እየገለጹ ነው።
በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች ከሚሰጡት አስተያየቶች በተጨማሪ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በመደውል አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ ግለሰቡ ከመነሻቸ ጠንካራ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው በመሆኑ፣ ከዚህ ያለፈ እንዲናገሩ አይጠበቅም ብለዋል
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አንድን ህዝብ በዚህ ሁኔታ ማዋረዳቸው ተገቢ አለመሆኑንና የኢትዮጵያ ህዝብ ለለውጥ መነሳቱን ገልጿል።
የሰሜን ወሎ የመኢአድ ጽህፈት ቤትም የም/ል ፕሬዚዳንቱን ንግግር አጥብቆ በመኮነን አቶ አለምነው የተናገረው የስርአቱ ፖሊሲ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅም የሰሜን ወሎ መኢአድ ጽህፈት ቤት አሳስቧል።
ሌላ አስተያየት ሰጪም እንዲሁ ለአማራው በባዶ እግሩ መሄድ መንስኤው እርሳቸውና እርሳቸውን የመሰሉ ሰዎች ናቸው ብለዋል