በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረሱል እያሉ ነው

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ኖርዌይ በተገኙበት ወቅት የገጠማቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ  በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን  ሰደተኞች  በጃንዋሪ  26/2012 አስገድዶ የመመለስ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በኖርዌይ መንግስታት መካከል መፈረሙ ሲቃወሙ መቆየታቸውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ አስታውሶአል።

ስምምነቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያንንን በሀይል በማስገደድ ወደ አገራቸው እንደሚለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እኤአ ማርች 16 እንደሚጀመር ጠቅሶ፣  ኢትዮጵያኖችም በአለማቀፍ ደረጃ ማርች 12 በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንዲገኙ ማህበሩ ጥሪ አቅርቦአል

የኖርዌይ እና የመለስ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንካራ ወዳጅነት እየመሰረቱ መምጣታቸው ይነገራል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide