መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በቢቸና አውራጃ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2 የቀድሞ የቅንጅት አባሎች ተገድለዋል። ገዢው ፓርቲ እንዳደራጀ የሚነገረው ቡችሌ
የተባለው ቡድን ክንዳየ አለሙና አባይነህ በተባሉ የቀድሞ የቅንጅት አባላት ላይ ስዋ ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግድያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ሁለቱም ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ
አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበው መሞታቸው ታውቛል።
ከ10 ቀናት በፊት በሻሸመኔ ከተማ አንድ ተመራቂ ተማሪ ክፉኛ ተደብድቦና በጩቤ ተወግቶ ከሞተ በሁዋላ በትናንትናው እለት ደግሞ በዚሁ ከተማ 81 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው
ያልታወቁ ሰዎች ሶስት ሆነው ይጓዙ ከነበሩ ሴቶች መካከል አንደኛዋን አፍነው ወስደው ከደፈሯትና በሳንጃ ከወጓት በሁዋላ በአሁኑ ሰአት ሻሸመኔ ፖሊ ክሊኒክ እንደምትገኝ ታውቋል፡፤ በሻሸመኔ
መናሃሪያም አንድ ሾፌር በጩቤ ተወግቶ በክምና ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ ዲዲሲ ኦቨርስሲስ እየተባለ በሚጠራው የቻይና ኩባንያ ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት የቀድሞ ወታደሮች እስከነመሳሪያቸው ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ
መጥፋታቸው ታውቋል። ወታደሮቹ ስልክ ሲደወልላቸው ” ድሮው መከላከያ አሰቃይቶን ነው የወጣነው፣ አሁንም ቻይና እያሰቃየን ነው፤ እኛ ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል ሄደናልና እኛን ለሜአዝ
አትድከሙ” ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።