ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የተነሳው የህዝብ ተቃውሞ እየተስፋፋ በመሄዱ የአገሪቱ ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል።
ተቃዋሚዎቹ በመጀመሪያ ያነሱት ጥያቄ ከመንግስት በኩል ምላሽ ቢያገኝም፣ ህዝቡ ግን ሙስናን ለመዋጋት በቂ እርምጃ አልተወሰደም እንዲሁም ለሚቀጥለው አመት ለአለም ዋንጫ ዝግጅት የሚመጣው ወጪ በዝቷል በሚል ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው።
በ100 የአገሪቱ ከተሞች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሰልፉ ላይ መሳተፉ ታውቋል።