በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያውያን ነጻነት ፈላጊዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008)

በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ እየተላለፈ ያለው የፖለቲካ ውሳኔ፣ ከኤርትራውያን ባሻገር ኢትዮጵያውያን ለውጥ ፈላጊዎች ጭምር ኢላማ ያደረገ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ የኤርትራው ባለስልጣን ገለጹ። በእኛ በኩል የምንችለውን እያደረገን እንገኛለን ያሉት አቶ የማነ ገብረዓብ፣ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ አባላት ኤርትራን በተመለከተ ያወጡትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሪፖርት በተመለከተ ከኢሳት ጋር ቃለ-ልልስ የደረጉት አቶ የማነ ገብረዓብ የኤርትራ ጥንካሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የሚኖረውንም ጠቀሜታ አንስተዋል።

የኢትዮጵያውያን ትግል መዳከምም በተመሳሳይ ኤርትራ ላይ ጫና እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

የኤርትራው ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪና የህግደፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ የማነ ገብረዓብ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውም ትግል እንዲሳካለት ተመኘተው፣ ለስኬቱ መደጋገፍ እስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል።