ታኀሳስ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንደቀሰቀሰው በሚነገረው ግጭት ከትናንት ጀምሮ ከ10 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የጎንደር መተማ መንገድ በመዘጋት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።
የመንግስት ካድሬዎች በቅማንትና አማራ መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ሰሞኑን ካድሬዎቹ መሳሪያ ታጥቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምንም እንኳ ህገመንግስቱ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል የሚደነግግ ቢሆንም፣ ካድሬዎች ሆን ብለው መሳሪያ እየታጠቁ ትንኮሳ ማድረጋቸው፣ ለግጭቱ መነሳት ምክንያት ሆኗል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
የገዢው ፓርቲ የጸጥታ አስከባሪዎች ግጭቱን ከቀሰቀሱ በሁዋላ ከዳር ሆነው መመልከታቸው የአካባቢውን ነዋሪዎች አሳዝኗል።