ሚያዝያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ስም የተያዙ የንግድ ድርጅቶች በግሉ ዘርፍ መከናወን ያለባቸውን ስራዎች ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ መሻማታቸው፣ በግሉ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ መምጣታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
የመከላከያን መስረተ ልማቶች ለማሟላት በሚል በልማት ድርጅትነት ራሱን ችሎ የተቋቋመው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በመውጣት ልማትን ለማገዝ በሚል ሽፋን ከግሉ ዘርፍ ጋር እየተወዳደረ በንግድ ስራ ላይ መሰማራቱ ተገቢ አለመሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሲመሰረት የመከላከያ ሠራዊት መኖሪያ ቤቶች፣ ቢሮዎች እና ከመከላከያ ስራዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ግንባታዎችን ለማከናወን ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ወደ ንግዱ ዓለም በመግባት እና የአንደኛ ደረጃ ስራ ተቋራጭነት ፈቃድ በማውጣት
ለግሉ ዘርፍ የሚወጡ ስራዎችን በብዛት እየተሻማ መውሰዱ የግሉ ዘርፍ እንዲዳከም የራሱን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢንተርፕራይዙ በግል ዘርፍ በቀላሉ ሊሰሩ የሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በአዲስአበባ፣ በድሬዳዋ፣ በባህርዳር በመቀሌና
በሽሬ ከተሞች በመገንባት ላይ ሲሆን፣ የተለያዩ የመንግስት ፕሮጀክቶችን በትዕዛዝ ጭምር በማግኘት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡
ኢንተርፕራይዙ እንደነጋዴ የሚቀጥል ከሆነ በየትኛውም እሱ በሚሳተፍበት ጨረታ ለመሳተፍ እንኳን ሞራል እንደማይኖራቸው የዘርፉ ምንጮችን ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት ተችሎአል፡፡
በህወሃት የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች የሚመራው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በቢሊየን ብር የሚገመት ፕሮጀክቶችን በትዕዛዝ በመውሰድ በአባይ ግድብ፣ በስኳር እና በማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ላይ እየሰራ ነው። ኮርፖሬሽኑ አውቶቡስና ሌሎች ተሸከርካሪዎችን በመገጣጠምና ያለ ውድድር በመሸጥ ስራ ውስጥ መግባቱ ፣ በሀገር ውስጥ በተመሳሳይ ስራ ላይ ይገኙ የነበሩ እንደሆላንድ ካር ያሉ ጠንካራ ተቋማት ከስረው እንዲዘጉና ከገበያ እንዲወጡ ማድረጉ ይታወቃል።
መንግስት ፕሮጀክቶችን ያለውድድር ለመከላከያ ተቋራጮች መስጠቱ ሕገወጥ ነው ያሉት ምንጮቹ ፣ የመንግስት ግዥ ከመንግስት ተቋማት መከናወን አለበት የሚለው የግዥ መመሪያ ከነጻ ገበያ መርህ አንጻር የማያስኬድና የግሉን ዘርፍ ዕድገት የሚገታ፣ በውድድር ሊገኝ
የሚችል ጥራትንና የገንዘብ ቅናሽን የሚያስቀር በመሆኑ የሀገር ሐብትን ለብክነት የሚዳርግ አሰራር ነው ሲሉ ተችተውታል።
ኢንዶውመንት በመባል የሚታወቁ ፣ ሱር ኮንስራክሽን፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ፣ መሶበ ሲሚንቶ፣ ሜጋኔት ኮርፖሬሽን፣ ጉና የንግድ ሥራዎች፣ ራዲዮ ፋና፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ የራዲዮፋና እና የዋልታ ጥምረት የሆነውና በማስታወቂያና ፕሮሞሽን ችርቻሮ ውስጥ
የሚሰራው ዋፋ ኩባንያ፣ አምባሰል የንግድ ስራዎች፣ ዳሸን ቢራና ሌሎችም የኢህአዴግ የንግድ ድርጅቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በንግዱ ውስጥ እጃቸውን በማስገባት ተገቢ ያልሆነ ውድድር ከመፍጠር አልፈው በህጋዊ መንገድ ግብር ከፍለው፣እርስበርስ ተወዳድረው ሥራ
የሚያገኙ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪም ተጽዕኖ መፍጠራቸው እንደማሩ ብረታብረት፣ ተሻለ ጋራዥ፣በርታ ኮንስትራክሽንና የመሳሰሉ አንጋፋ ድርጅቶች