ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን 300 ስደተኞችን መያዝዋን ሱዳን አስታወቀች።
ስደተኞቹ የሳህራ በርሃን አቋርጠው ወደ ሊቢያ በመግባት በባሕር ወደ አውሮፓ ለማቅናት ሲጓዙ እንደነበር የሱዳን ልዩ ጦር የጸጥታ ሹም ጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ገልጸዋል። በሰሜናዊ ሱዳን አል ሸቨርሊት ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ አብዛሃኞቹ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን መሆናቸውንም አስታውቀዋል።። የሱዳን መንግስት በቅርቡ ከአውሮፓ ኅብረት የሕገወጥ ስደተኞችን ፍልሰት ለመቆጣጠር 100 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ እንዳገኘ ሱዳን ትሪቢውን አክሎ ዘግቧል።