ሰማያዊ ፓርቲ የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ

ሚያዚያ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 19 በአዲስ አበባ የተካሄደ ውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን በሰልፉ  ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት አመራሮች እና ደጋፊዎች  በብዛት መገኘታቸውን ገልጿል።

ወጣቶቹ የነበራቸው ጽናት የሚገርም ነበር ያለው ዘጋቢያችን፣ ፖሊስ በሰልፉ ላይ ህዝብ በብዛት እንዳይገኝ ለማድረግ ያሰበው እቅድ አለመሳካቱንም ገልጿል።

ሰልፈኞች በርካታ ፖሊቲካዊና ማህበራዊ ጥያቄዎችን እያነሱ ሲጠይቁ መመልከቱንም ገልጿል።

ሰማያዊ ፓርቲ ከ25 በላይ አመራሩና አባላቱ ታስረውበት ያደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በስኬት መጠናቀቁ ያስደሰታቸው ወጣቶች ስሜታቸውን በማህበራዊ ድረገጾች እየገለጹ ነው።