ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ፑቲን ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ዩክሬን ያልከፈለችውን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ ባለመክፈሉዋ ነው።የሩሲያ ታላቁ ነዳጅ ማከፋፈያ ድርጅት ጋዝ ፕሮም ዩክሬን በአስቸኳይ እዳዋን የማትከፍል ከሆነ የነዳጅ አቅርቦቷ ይቋረጥባታል። የዩክሬን የነዳጅ አቅርቦት መቋረጥ ከሲሶ በላይ የነዳጅ ፍጆታቸውን ከሩሲያ የሚያገኙት የአውሮፓ አገራት አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ።
አሜሪካ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ የተቸች ሲሆን፣ የጀርመንና የፈረንሳይ ኩባንያዎች ደግሞ ጋዝ ወደ ዩክሬን ለማከፋፈል ሙከራ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በዩክሬን ምስራቃዊ ግዛት የተነሳው አመጽ እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ የአገሪቱ መንግስት፣ ለነዋሪዎች ከፍተኛ የአስተዳደር ነጻነት እንደሚሰጥ አስታውቛል።
ሩሲያ በበኩሉዋ ዩክሬን በፌዴሬሽን እንድትዋቀር አበክራ እየጠየቀች ነው። የዩክሬን መንግስት እርምጃው ዩክሬንን የሚያፈራረስ ነው በማለት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።