ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘነበ አባት አቶ በላይ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ልጃቸው ከጨጓራ ህመም ውጪ የልብ ድካምም ሆነ ድንገት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ እንዳልነበረበት ጠቅሰው፤ እስካሁን ድረስ ምን ሆኖ እንደሞተ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በሀዘን ስሜት ተውጠው ተናግረዋል።
ቡና ከሃዋሳ ከነማ ጋር ላለው ግጥሚያ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ወደ ሃዋሳ ሲያመራ አብሮ እንደተጓዘ ለረዥም ጊዜ ሳይመለስ መቅረቱና ድምጹ መጥፋቱ የቤተሰቡን አባላት እጅግ አስጨንቋቸው መቆዬቱን ያወሱት አቶ በላይ፤ቡድኑ ጨዋታውን አጠናቅቆ ሲመለስ ልጃቸው መቅረቱ እጅግ ሢያሳስባቸው መክረሙን ጠቅሰዋል።
ጓደኞቹ በቅርቡ የዘነበን መሰወር ማሳወቃቸውን ተከትሎ በተደረገ ፍለጋ ልጃቸው በሀዋሳ ተቀብሮ ሬሳው መገኘቱን ሢሰሙ ቤተሰቡ በመላ ሊቆጣጠሩት ባልቻሉት ከፍተኛ ድንጋጤና ሀዘን ውስጥ መውደቃቸውን አቶ በላይ እያለቀሱ ይናገራሉ።
በምን ምክንያት እንደሞተ ወይም ማን እንደገደለው ግን እስካሁን የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን የገለጹት አቶ በላይ፤ ከሀዋሳ አስከሬኑ ወጥቶ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ሲቀበር አስከሬን የእሱ እንደሆነ መታወቁን፣ ሆኖም ምን ሆኖ እንደሞተ የምርመራ ውጤቱን እስካሁን እንዳልሰሙና ከሦስትና አራት ቀናት በኋላ ይነገርዎታል ተብለው እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የወጣት ዘነበ በላይ ሁለተኛው የቀብር ሥነ ስርዓት ባለፈው አርብ በቀጬኔ መድኃኒ ዓለም ቤተክርስቲያን እጅግ በርካታ የቡና ክለብ ደጋፊዎችን ጨምሮ ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት በድምቀት መፈጸሙ ይታወቃል። “ልጃችንን እና ጓደኛችንን በላይን ማን ገደለው? “ የሚለው ጥያቄ በቀብሩም ላይ የበርካታ ለቀስተኛ ቁጭትና መነጋገሪያ ነበር።
የልጃቸውን ድንገት ማለፍ ተከትሎ ህዥቡ ላሳያቸው የሞራል ድጋፍና ማጽናኛ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ በላይ ከክለቡም ሆነ ከክለቡ ደጋፊዎች በገንዘብ በኩል ድጋፍ ተደርጎላቸው እንደሆነ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በገንዘብ በኩል እስካሁን የተደረገላቸው ድጋፍ አለመኖሩን