ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ዜጎች ያለፍላጎታቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉ አለማቀፍ ህግንና ህገመንግስቱን መጣስ ነው ሲሉ ሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ ተናገሩ
ሚስተር ቤን ራውለስን ለኢሳት እንደገለጡት በታችኛው የኦሞ ሸለቆ አካባቢ ለስኳር ልማት በሚል ዜጎች እንዲፈናቀሉ የሚደረጉት ያለፍላጎታቸው ነው። አለማቀፍ ህግም ሆነ የኢትዮጵያ ህገመንግስት አርብቶአደሮች ያለፍለጎታቸው እንዲፈናቀሉ አይፈቅድም በማለት የተናገሩት ራውለንስ ሂውማን ራይትስ ወች የኢትዮጵያ መንግስትም ለህጎቹ እንዲገዛ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች በፍላጎታቸው እንደሚነሱና እንደሚሰፍሩ ይገልጣል፣ ሂውማን ራይትስ ወች በምን መረጃ ላይ ተንተርሶ ነው፣ ዜጎች ያለፍላጎታቸው እየተፈናቀሉ ነው የሚል ጥናት ያቀረበው የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ቤን ራውለንስ ” እኛ ያለን መረጃ የሚያሳየው ዜጎች ያለፍላጎታቸው እየተነሱ መሆኑን በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ አቅርበናል፣ እኛም እኛ ያቀረብነው መረጃ መንግስት ከሚለው ጋር የሚጻረር ነው”” ብለዋል።
መንግስት ሂውማን ራይትስ ወችን ጸረ ልማት ነው በማለት ይከሳል ለዚህ ምን መልስ አለዎት ለተባሉት ደግሞ ” ጸረ ልማት እንደምንባል እናውቃለን፤ ያ ችግር የለውም ነገር ግን ልማት እና የመልማት መብት ምን ማለት እንደሆነ ልናውቅ ይገባናል። የኢትዮጵያ ህገመንግስት ዜጎች የራሳቸውን ልማት በምን መንገድ መካሄድ እንዳለበት የመምረጥ እድል ሰጥቶአቸዋል፤ ይህ ማለት ሰዎች መማከር አለባቸው፣ መሬታቸውን ለስኳር ልማት የምታውልም ከሆነ ካሳ መክፈል አለብህ በማለት” መልሰዋል።
በቂ ምክክር ሳያደርግ ወይም ተገቢውን የካሣ ክፍያ ሳይፈጽም በመንግስት የሚካሄድ የስኳር ልማትን ለማስፋፋት የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ የታችኛው የኦሞ ሸለቆ ነዋሪ የሆኑ አርብቶ አደሮችን በግዳጅ እያፈናቀለ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ትናንት ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide