የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደቡብ፣ አማራ እና ድሬዳዋ ዘጋቢዎች እንደገለጡት መንግስት ህዝቡን ለመቆጣጠር በቀየሰው አንድ ለአምስት አደረጃጀት በመጠቀም ፣ አርሶአደሩን እና በተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎችን በግዳጅ በሳምንት ለሶስት ቀናት የእርከን ስራ እንዲሰሩ እያደረገ ነው።
አርሶአደሩ እንዳሉት እርሳቸው በሚሩበት በቦረና ዞን የተለያዩ ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ታስረው መገኘታቸውን በዝርዝር ገልጠዋል
አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የግብርና ባለሙያ እንደተናገሩት ከሶማሊ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ የግዳጅ የእርከን ስራ በመካሄድ ላይ ነው።
አርሶ አደሩ የእርከኑን ስራ በአወንታዊ መልክ እንዳልተቀበለው የገለጡት እኝሁ ሰራተኛ፣ የግዳጅ ስራው ዋና አላማ ህዝቡ ሌሎች ነገሮችን እንዳያስብ በስራ መወጠር ነው።
አርሶአደሩ የሚያሰማውን እሮሮ በተመለከተ የመንግስት ባለስልጣናት እስካሁን የተናገሩት ነገር የለም።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide