መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት መሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ መኮንን ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት ከጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየጠፋ ያለው ሰው ህይወት
መንግስት መፍትሄ ሊሰጠው ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው።
በጅንካ ነዋሪ የሆነው ኡመር ንጋቱ በሙርሲ ብሄረሰብ አባላት በጥይት ተደብድቦ እንደሞተ መነገሩን ተከትሎ ሃሙስ እለት ከቀብር መልስ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን፣ ከሰአት በሁዋላ የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው በብዛት ተሰማርቶ ታይቷል።
ሹፈሮች የእርሻ ስራው ወደሚካሄድበት አካባቢ ለመጓዝ መፍራታቸውን ለመስተዳድሩ ቢያመለክቱም እስካሁን የተሰጣቸው ማስተማመኛ የለም።
መንግስት ችግሩን እንዲፈታ በተደጋጋሚ በፓርቲያቸው ቢጠየቅም፣ የችግሩ ፈጠሪዎች እናንተው ናችሁ በሚል እንዳልተቀበሉት አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።