መቀሌ በውሃ ጥም ውስጥ ናት

ታህሳስ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ መቀሌ በውሃ ጥም እየተመታች መሆኑዋን ኗሪዎቿ ተናገሩ፡፡ ላለፉት አራት ወራት በሳንምንት አንድ ቀን በወረፋ የምትደረሰው ውሃ ሌሊቱን ሁሉ ስትጠበቅ ታድራለች፣ እንደነዋሪዎች አነጋገር።

ከተማ አሰተዳደሩ በበኩሉ ከእርዳታ ድርጅቶች በቂ ገንዘብ በማፈላለግ  በሚቀጥለው አመት የውሃ አቅርቦቱን ለማሻሻል እንሰራለን ብሎአል፡፡ አስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸው የዕርዳታ ድርጅቶችን  ከመጠበቅ ለትሃድሶ እያለ ለግብዣ ከሚያወጣው በመቆጠብ ማሰራት እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡

የህወሀት ንብረት የሆነው ኢፈርት የከተማዋን የውሃ ግንባታ  ከመንግስት ጋር በሽርክና ለመስራት እየተደራደረ ነው፡፡ የውሃ ዘርፉ ለኢፈርት ይሰጥ አይሰጥ በሚል ክርክር ለሁለት የተከፈለው የትግራይ ክልል ካቢኔ፣ ክርክሩን ወደ  ፌደራል መውሰዱንም ዘጋቢአችን ገልጿል።