ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ የጁባ የሰላም አስከባ ሃይል አዛዥ ሆኑ

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል በአብየ አዛዥ የሆኑት ሌ/ጄ/ዮሃንስ ገብረመስቀል በደቡብ ሱዳን የሚመሰረተውን የሽግግር መንግስት ሂደት እንዲመሩ ተሹመዋል። ከ100 ያላነሱ ወታደሮች ደቡብ ሱዳን የገቡ ሲሆን፣ አዛዡም ጁባ መግባታቸው ታውቓል።

ጄ/ል ዮሃንስ በወር ከ20 ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ  እንደሚከፈላቸው የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአዲስ አበባ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት በደቡብ ሱዳን አዲስ የሽግግር መንግስት ይመሰረታል።