ህገ ወጥ አሰራሮችን ያጋለጡ መምህራን ታሰሩ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ስሙ ቤላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የህብረት ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የሆኑት መ/ር ጥላሁን በዙ እና መ/ር አዳም ዘውዱ በት/ቤቱ እየተከናወነ ያለዉን ህገ-ወጥ አሰራር በመቃወማቸው እንዲሁም ለፌደራሉ ፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ጥቆማ በማድረጋቸው፣ ወንጀል ሰርተዋል በሚል ከተጠረጠሩት ጋር አብረው እንዲታሰሩ መደረጉን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መምህራን ገልጸዋል።

የየካ ክ/ከተማ የመምህራን ልማት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሽመልስ መምህራኑ መታሰራቸውን አረጋግጠው፣ ለምን እንደታሰሩ  እንደማውያቁና ጉዳዩ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ የፖሊስን ምርመራ መጠበቅ እንደሚሻል ገልጸዋል።