መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ በአዲስ አበባና በአጎራባች ከተሞች ባሉ ቤቶች እየዞሩ ለመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ እያስገደዱ ነው። እድሮች በነፍስ ወከፍ ከ8 ሺ ብር ጀምሮ እንዲከፍሉ መመሪያ ተላልፎላቸዋል።
በዚህ መመሪያ የተሰላቹና የተበሳጩ ሰዎች “ወዴት እንሂድ” ሲሉ ለኢሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመለስ ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሊቀመንበርነት የሚመራ ሲሆን የአቶ መለስን አስከሬን በቋሚነት የሚያርፍበትን ቦታ የማዘጋጀትና ስራዎቻቸውን ለህዝብ የማቅረብ አላማ አለው።
ምንም እንኳ መንግስት ለፋውንዴሽኑ ማሰሪያና ስራ ማስኬጃ በየአመቱ ገንዘብ የሚሰጥ ቢሆንም፣ ይህ ሳያንስ እያንዳንዱ ህዝብ ገንዘብ እንዲያወጣ መገደዱ አግባብ አለመሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ገንዘብ መስጠትም ካለባቸው የኢህአዴግ ደጋፊዎች እንጅ ኢህአዴግን የማይደግፉት እንዲሰጡ መገደድ የለባቸውም ሲሉ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በእድሮች ላይ ሳይቀር የተጣለው የመዋጮ ግዴታ በበርካታ የእድር አባላት ላይ ቀርታ ፈጥሯል።