የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በማስፈራሪያ መቀጠሉ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 7/2010) ዕሁድ የተጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በውዝግብ እና በሕውሃት ማስፈራሪያ መቀጠሉን ምንጮች ገለጹ።

ፋይል

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በ4 ድርጅቶች ስምምነት የወጣ ነው መባሉም በስብሰባው ላይ ተቃውሞ ቀስቅሷል።

ቀደምቶቹን የሕውሃት መሪዎችን በብዛት ወደ ስብሰባው በማስገባት ተጽዕኖ ለማሳረፍ የተደረገው ጥረት የተፈለገውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ በስብሰባው አዳራሽ አካባቢ የጦር ጄኔራሎች ታይተዋል።

ጡረተኞቹ እና በስራ ላይ ያሉት ጄኔራሎች ከደህነንት ሃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ  እና ከአቶ  በረከት ስምኦን ጋር መገናኘታቸውም ታውቋል።

የኦህዴድ እና አንዳንድ የብአዴን መሪዎች  ጠንካራ አቋም ይዘው መሟገታቸውም ተሰምቷል።

ስብሰባው በቀናት እንደሚጠናቀቅ እየተገለጸ ሲሆን፣የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀመርም ተመልክቷል።

የሕወሃት ሰዎች ተደራጅተው በኦሕዴድ እና በብአዴን  አንዳንድ አመራሮች ላይ ጫና ለማሳረፍ የተንቀሳቀሱበት ይህ ስብሰባ ፣ከተጠበቀው በላይ ጥያቄና ተቃውሞ እንደተነሳበትም ተሰምቷል።

የወልቃይት እና የአማራ ክልል ለም መሬቶች ወደ ሌላ ክልል መካለላቸው ወይንም መወሰዱ ለክልሉ ሰላምም ሆነ ለዕድገታችን እንቅፋት ሆኗል የሚለው በብአዴን  በኩል ተነስቷል።

የህዳሴውን ግድብ ስራ በበላይነት የሕወሃት  ሰዎች ብቻ እንዲይዙት መደረጋቸው እና የመቶ ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ኦዲት ተደርጎ  አለማወቁ  እንዲሁም ሕውሃት ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር  ያለው የተለየ ግኑኝነትም ጥያቄ ተነስቶበታል።

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን በተመለከተ የኢሕአዴግ አባል ድርጅት እንዲሆኑ በአቶ በረከት ስሞኦን የቀረበው ሃሳብ በኦህዴድ እና  ብአዴን ተቃውሞ ገጥሞታል፥፡

ያለነው አንድ መሆን አቅቶን እየታመስን ፣ሌሎችን ወደ አባልነት የማምጣቱ ዓላማ ምንድ ነው ሲሉ መጠየቃቸውና መቃወማቸው ተመልክቷል።

ስብሰባውን እንደጠበቁት አቅጣጫ ማስያዝ ባለመቻላቸው የህወሃት መሪዎች በተለይም  አቶ አባይ ጸሃዬ እንዲሁም አቶ በረከት ስምኦን እያስፈራሩ መሆናቸውም ታውቋል።

ቀደምቶቹን የሕወሃት መሪዎች በብዛት ወደ ስብሰባው በማስገባት ተጽዕኖ ለማሳረፍ የተደረገው ጥረት የተፈለገውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ በስብሰባው አዳራሽ አካባቢ  የጦር ጄኔራሎች ታይተዋል።

ጡረተኞቹ እና በስራ ላይ ያሉት ጄነራሎች ከደህነንት ሃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ  እና ከአቶ  በረከት ስምኦን ጋር መገናኘታቸውም ታውቋል።

ስብሰባው በቀናት እንደሚጠናቀቅ እየተገለጸ ሲሆን፣የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀመርም ተመልክቷል።

አቶ አባይ ጸሃዬ ምርጫችን  ሁለት ነው፡ አንድም ችግር ፈጣሪዎቹን የብአዴንና የኦህዴድ ሰዎችን ከኢሕአዴግ ወስጥ ማስወገድ አሊያም ኢሕአዴግን ማፍረስሲሉ መዛታቸው ተመልክቷል።

የአስቸኳይ ግዚ አዋጁ የታወጀው  በአራቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ስምምነት ነው እየተባለ የሚሰጠው መግለጫም ተቃውሞ ቀርቦበታል ሲሉ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።

መቼ ተስማምተን ያሳለፍነው ውሳኔ ነው የሚለውን የሕወሃት መሪዎች ተጠይቀዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአራቱ ድርጅቶች ስምምነት መታወጁን  ከተናገሩት ውስጥ የሕወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል  ይገኙበታል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ተቃውሞዋን ለገለጸቸው የዩ.ኤስ. አሜሪካ ልኡካን ማብራሪያ የሰጡት አቶ ስብሃት ነጋ፣አቶ ስዩም መስፍን እና አቶ አባይ ጸሃዬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታወጀው የወታደሩን ጣልቃገብነት ለመከላከል ነው ሲሉ መናገራቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።   ፡፡