የህውሃት ካድሬዎች ትንኮሳ እንዲቆምላቸው የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡

የህውሃት ካድሬዎች ትንኮሳ እንዲቆምላቸው የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) የህገ መንግስቱን አንቀጾች በትክክል መተርጎም በማይችሉ የህውሃት ካድሬዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ቀኖና የሚደረጉ ትንኮሳዎች ይቆምላቸው ዘንድ የእምነት አባቶች ጠየቁ፡፡
በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በመላው ዓለም የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የሚገለገሉበት የቃልኪዳን ቀለም የያዘ ምልክት የስርዓቱ ካድሬዎች እንደ ባንዲራ በመቁጠር የእምነቱ ተከታዮችን በተለያዩ ጊዜ ለማሰማቀቅ፣ለመደብደብና ለማሰር የሚጠቀሙበት መሆኑን አባቶች ተናግረዋል፡፡
“ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የእምነቱ ተከታዮች የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው” በማለት የዕምነቱን ተከታዮችና አባቶች የሚኮንኑት በአማራ ክልል የስልጣን እርከን የጨበጡት የህውሃት ሰው “በህገ መንግስቱ የተደነገገው ‘አንቀጽ 8’ የተገለጸውን ‘የሰንደቅ ዓላማ አርማ መቀየር አይቻልም’ የሚለውን ድንጋጌ ቤተ ክረስቲያኗ ጥሳለች” በማለት ይከሳሉ፡፡
የህውሃቱ ሰው በተናገሩት ንግግር ያልተደሰቱት በስብሰባው የተገኙ የተለያዩ እምነት ተከታይ አባቶች ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን ፤ሰንደቅ ዓላማን የሚመለከተውን የህገ መንግስት ድንጋጌ አንቀጽ ሶስት ላይ መሆኑን አንኳን ያለዩት የህውሃት ሰው በደንጋጌው ቁጥር ሶስት ላይ ስለ ተቋማት ምልክት የሚመለከተውን ድንጋጌ ኢህአዴግ አላከበረም በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ ውይይት ላይ ከተገኙ የእምነት አባቶች መካከል ለተሰጠው ትንኮሳ ምላሽ የሰጡት አባት እንደተናገሩት “እንደ ኦርቶዶክስ ዕምነት ሰንደቅ ዓላማ የሚል አማርኛ በቤተ ክርስቲያናችን የለም” ብለዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማ የሚለውን ቋንቋ የሚጠቀሙት እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው መሆኑን የሚነገሩት የዕምነቱ አባት በቤተ ክርስቲያናቸው አረንጉዴ፣ቢጫና ቀይ የያዘው ዓርማ የ”ቃል ኪዳን ምልክት” ሚል መሆኑን አስረግጠው ገልጸዋል፡፡
እንደ ቤተክርስቲያን ደመና ሲመጣ ከምድር እስከ ሰማይ የሚዘረጋው የቀስተ ዳመና ምልክት እንደ ቃልኪዳን ተቀብለው መለያውን ይዘው በሚከበሩ ክብረ በዓላት እንደሚመጡ የተናገሩት አባት ምልክቱን ለፖለቲካ ትርፍ አለመሆኑ ሊታዎቅ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ይህን የቃል ኪዳን ምልክት ከቤተ ክርስቲያኗ የአምልኮ ቀኖና ጋር ለመለያየት የሚደረገውን አካሄድ የተቃወሙት አባት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት በሙሉ ተቀባይነት ያለው ምልክት በመጠቀማችን እንደ አመጸኛ ተቆጥረን ጫና ሊደረግብን አይገባም በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡