ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 7/2011)የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀብራቸው ስነስርዓት በዩጋንዳ በብሄራዊ ጀግና የክብር ስነስርዓት እንደሚፈጸም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ አየር ሃይል የሀገሪቱን ከፍተኛ የጀግንነት የክብር ኒሻን ካገኙት ጥቂት ሰዎች አንዱ የሆኑት ኮለኔል ጌታሁን ካሳ በስደት ለሚኖሩባት ዩጋንዳ አየር ሃይል ከፍተኛ ተግባር በመፈጸማቸ የዩጋንዳ መንግስት ልዩ ክብር እንደሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1977 ጀምሮ በሄሊኮፕተር አብራሪነት የቆዩት ኮለኔል ጌታሁን ታላላቅ የውጊያ ግንባሮች ላይ በመሰለፍ ለሀገራቸው ዳር ድንበር መከበር ከፍተኛ ተጋድሎዎችን መፈጸማቸውን ከህይወት ታሪካቸው ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ ኮለኔል ጌታሁን ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀብራቸው ስነስርዓት በዩጋንዳ በብሄራዊ ጀግና የክብር ስነስርዓት እንደሚፈጸም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ አየር ሃይል የሀገሪቱን ከፍተኛ የጀግንነት የክብር ኒሻን ካገኙት ጥቂት ሰዎች አንዱ የሆኑት ኮለኔል ጌታሁን ካሳ በስደት ለሚኖሩባት ዩጋንዳ አየር ሃይል ከፍተኛ ተግባር በመፈጸማቸ የዩጋንዳ መንግስት ልዩ ክብር እንደሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1977 ጀምሮ በሄሊኮፕተር አብራሪነት የቆዩት ኮለኔል ጌታሁን ታላላቅ የውጊያ ግንባሮች ላይ በመሰለፍ ለሀገራቸው ዳርድንበር መከበር ከፍተኛ ተጋድሎዎችን መፈጸማቸውን ከህይወት ታሪካቸው ለማወቅ ተችሏል።

ኮለኔል የተወለዱት በቀድሞ የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት በሚል ሲጠራ በነበረው አከባቢ ነው።

በ1943 ዓመተ ምህረት በአለታ ወንዶ የተወለዱት ኮለኔል ጌታሁን ካሳ እዚያው አለታ ወንዶ በሚገኘውና በቀድሞ አጠራሩ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ጀመሩ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ ይርጋለም በሚገኘው ራስ ደስታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

የሃረር የመኮንኖች አካዳሚን በ1962 የተቀላቀሉት ኮለኔል ጌታሁን የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመግባት የአብራሪነት ስልጠና ወስደዋል።

በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረትም ተልከው ከፍተኛ የአብራሪነት ትምህርት መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ኮለኔል ጌታሁን ኢህ አዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር በኬኒያ በኩል ስደት መውጣትቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ከኬኒያ በቀጥታ ወደ ዩጋንዳ ኤንቴቤ በማምራት በአብራሪነት ሙያቸው የዩጋንዳን መንግስት አገልግለዋል።

የዩጋንዳ መንግስት ከአማጺ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ውጊያዎች በተለያዩ የጦር ሄሊኮፕተሮች በመሳተፍ ከፍተኛ ጀግንነት መፈጸማቸውን የዩጋንዳ መንግስት ካሰራጨው ጽሁፍ ለመረዳት ተችሏል።

ኮለኔል ጌታሁን እንደሁለተኛ ሀገራቸው በሚቆጥሯት ዩጋንዳ ህይወታቸው ያለፈው ባለፈው ሳምንት መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የቀብራቸው ስነስርዓት በብሔራዊ ደረጃ በከፍተኛ ክብር እንዲፈጸም የዩጋንዳ መንግስት መወሰኑም ታውቋል።