ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣

ሚያዚያ 22 ቀን 2002 ዓም

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቀደም ሲል የሥርጭት አገልግሎቱን በኤፕሪል ወር መጨረሻ  እንደሚጀምር ይፋ አድርጎ ነበር።
የቴሌቪዥን አገልግሎቱ በኤፕሪል ወር መጨረሻ ሥርጭቱን ለመጀመር ዕቅድ ሲያወጣ በጊዜው ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን ታሳቢ
በማድረግ ነበር።

የመጀመሪያው፣ ሥርጭቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ማናቸውም ዓይነት የራሱ ውስጣዊ ዝግጅቶች ማጠናቀቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው፣
ፕሮግራሞቹን ለማስተላለፍ የሚያስችለው ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የሚደረግ የሁኔታ ማመቻቸት ነበር።

የመጀመሪያውን ዝግጅት በያዘው የጊዜ ሰሌዳ ሲያጠናቅቅ፣ ሁለተኛው እና የቴሌቪዥን ድርጅቱ ከሌሎች የመገናኛ ድርጅቶች ጋር
በሚገናኝባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጊዜው የነበሩን መረጃዎች በተወሰነ ደረጃ ለውጥ አሳይተዋል። ለዚህም ዋንኛው ምክንያት በዘመናችን
በከፍተኛ ፍጥነት የሚለዋወጠው የመገናኛ ቴክኖዎሎጂ ሁኔታ ነው። ከእነዚህ ለውጦች ጋር የሚጣጣም ማስተካከያ ለማድረግ

አሥፈላጊውን ሁሉ እያደረግን ቢሆንም፣ ቀደም ብሎ በያዝነው በኤፕሪል ወር መጨረሻ የጊዜ ሰሌዳ ሥርጭታችንን መጀመር አልቻልንም::

የሥርጭታችንን መጀመር በከፍተኛ ጉጉት ለሚጠብቀው በተለይ በሀገር ቤት ለሚገኘው ወገናችን ከፍተኛ ይቅርታ እየጠየቅን፣ በጥቂት
ተጨማሪ ቀናት ውስጥ አሥፈላጊውን የማስተካከያ ዝግጅት

አጠናቀን የሥርጭቱን መጀመሪያ ቀን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት፣

www.ethsat.com