ኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እየቀረጸች ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2011)ኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እየቀረጸች መሆኑ ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ እንደገለጹት በስራ ላይ ያለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስትራቴጂ የቆየና አላስፈላጊ ዝርዝሮችን የያዘ በመሆኑ ይቀየራል።

የነበረው ፖሊሲ ከውጭ ወደ ውስጥ የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው አዲሱ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ጥቅም ቅድሚያ በሚሰጥ መልኩ የሚቀረጽ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን በስራ ላይ ካለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በቀድሞ መንግስት የሚከተለው መስመር የተሻለና ዘርዘር ያለ እንደሆነም አመልክተዋል።