በእስራኤል የአንድ ኢትዮጵያዊ መገደልግጭት አስከተለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 23/2011)በእስራኤል የአንድ ኢትዮጵያ መገደልን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ግጭት አስከተለ።

ከሶስት ቀናት በፊት በቴለቪቭ በእስራኤል ፖሊስ ተተኮሶበት የተገደለው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በእስራዔል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል።

ለሁለት ቀናት ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ወደ ግጭት መቀየሩንም ለማወቅ ተችሏል።

በግጭቱ አምስት ኢትዮጵያውያን የተጎዱ ሲሆን ከእስራዔል ፖሊሶችም ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ፖሊስ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንን ማሰሩም ታውቋል።