በአዲስ አበባ አንድ በመሰራት ላይ ያለ ህንጻ ተደረመሰ

ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ጠዋት አያት ሰሚት አካባቢ ሞሃ ለስላሳ ፋብሪካ አጠገብ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ የተደረመሰ ሲሆን፣ በህንፃው ውስጥ የዳሽን እና አቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፎች ይገኙበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ አደጋው በስራ ሰአት ቢከሰት ኖሮ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር የገለጸው ዘጋቢያችን፣ አደጋው በየቀበሌው ያለው የግንባታ ቁጥጥር መስሪያ ቤት ብቃትና ሙስና ማሳያ ነው ሲል አስተያየቱን አስፍሯል።