ስታራቴክስ ኢንተርናሽናል ወርቅ ፈላጊና አምራች ኩባንያ ፈቃድ ተሰረዘ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 3/2010) ስታራቴክስ ኢንተርናሽናል የተባለው ወርቅ ፈላጊና አምራች ኩባንያ ፈቃድ መሰረዙን ኩባንያው ይፋ አደረገ።

በኢትዮጵያ አፋር አካባቢ ወርቅ በመፈለግና በማውጣት ሲንቀሳቀስ የቆየው ታኒ ስታራቴክስ ፈቃዱ እንዲታደስ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ መሰረዙን ኩባንያው አስታውቋል።

በሻኪሶ ዞን የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሜድሮክ ንብረት የሆነው የለገደንቢ ወርቅ አምራች ኩባንያ ፈቃድም መታገዱ ይታወሳል።

ኩባንያው ትላንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ ወርቅ በማፈላለግ ላይ የነበረው ስትራቴክስ ኢንተርናሽናል ውሉ እንደማይታደስ የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾለታል።

እስከ 2019 ፈቃድ ለማሳደስ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ባለመግኘቱ የኩባንያው ፈቃድ ተሰርዟል።