ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ኢትዮጵያውያን አፋጣኝ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 15/2011)በጌዲዮ ተፈናቃዮች ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን አፋጣኝ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ ጥሪ አደረገ።

የድርጅቱ አመራሮች ሰሞኑን በጌዲዮ ጉብኝት አድርገው ከተመለሱ በኋላ ለኢሳት እንደገለጹት ተፈናቃዮቹ ከደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት የበለጠ የስነልቦናው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

የግሎባል አሊያንስ ዳይሬክተር አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ችግሩ ጥልቅ ነው ኢትዮጵያውያን ከምን ጊዜውም በላይ ተረባርበው ለወገናቸው መድረስ አለባቸው ብሏል።

የሁለቱንም ወገኖች የሃገር ሽማግሌዎች አነጋግረናል ያለው ታማኝ በየነ ችግሩ በመንግስት ውስጥ ያሉ የፖለቲካ አመራሮች እንጂ የህዝቡ አይደለም ማለታቸውን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።