የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የመድረኩ አባላት እና የመድረኩ አስተዳዳሪዎች የድጋፍ ዝግጅት ያደረጉት ብቸኛው የኢትዮጵያ ሳተላይት  ቴሌቪዥን ህብረተሰቡን ለማገልገል የሚያደርገውን ጥረት በማድነቅ ነው።

በኢትዮጵያ የውይይት መድረክ ( ወይም ፓልቶክ) ከፍተኛ ተደማጭነትና ታዳሚ ያለው ኢካዲኤፍ ለኢሳት በተደጋጋሚ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል።

መድረኩ በተከታታይ ዝግጅቶች ተመሳሳይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱንም ከአስተዳዳሪዎች ለመረዳት ተችሎአል።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ  ከዚህ በፊት በተለያዩ አገራዊ እና ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ የገንዘብ ማሰባሰብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ከአስተዳዳሪዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢሳት ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ያለውን ከፍተኛ ምስጋና ለመግለጥ ይወዳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide