መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ም/ል ሊቀመንበር በመሆን በቅርቡ የተመረጡት የየኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ይህንን የተናገሩት ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የአክራሪነትና የሽብርተኝነት አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ አገሪቱን ሊበታትናት መቃረቡን ገልጠዋል። ” በሀይማኖት ሽፋን ኢትዮጵያን ለመበታተን ና ለማተራመስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ዝም ብለን መመልከት የለብንም፤ አሁን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ህገወጥ ቤቶችን ሰርታችሁዋል ተብለው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መፍትሄ አለማግኘታቸውን ተናገሩ
መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየካ እና በንፋስ ስልክ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ቤታቸው የፈረሰባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች አሁንም መጠጊያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው። በየካ አካባቢ የሚኖሩ አንድ ግለሰብ ለኢሳት እንደገለጡት ህጻናት፣ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች አሁንም መጠለያ አጥተው ቢቸገሩም መንግስት ግን ለችግራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። መሀንዲሶች ህጋዊ ነው ብለው በማጽደቃቸው ገንዘባቸውን አፍስሰው መሰረተ ልማቶችን መስራታቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ ...
Read More »ኢትዮጵያዊው የታክሲ ሾፌር ሩብ ሚሊዮን ዶላር ረስቶ ለወረደው ተሳፋሪ ገንዘቡን መለሰ
መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በላስ ቬጋስ የታክሲ ሾፈር የሆነው አዳም ወልደማርያም፣ አንድ በቁማር 250 ሺ ዶላር አሸንፎ ገንዘቡን ታክሲው ውስጥ ረስቶ ለወረደ ሰው ነው ገንዘቡን የመለሰው። አዳም ወልደማርያም በላፕቶፕ መያዢያ ውስጥ ታጭቆ ያገኘውን ገንዘብ እንዳተመለከተ ወዲያውኑ ለተቆጣጠሪው ማስረከቡን የደይሊ ሜል ሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል። ተሳፋሪው ገንዘቡን መልሶ በማግኘቱ መደሰቱንና ለወልደማርያምም 2 ሺ ዶላር እንደሰጠው ታውቋል። አዳም ገንዘቡን ...
Read More »የአትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምርጫ አልተሳካም ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያነጋገርናቸው ኢትዮጳያዊያን ሙስሊሞች ተናገሩ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንደተደረገ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን የዘገቡ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ግን ምርጫው አልተሳካም ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያነጋገርናቸው ኢትዮጳያዊያን ሙስሊሞች ተናገሩ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምርጫው በተጀመረ በጥቂት ሰኣታት ውስጥ ለምርጫው ከተመዘገበው 7 ሚሊዮን ህዝበ ሙስሊም ውስጥ 95 ከመቶው ድምጹን እንደሰጠ ሲናገሩ፤ ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው ሙስሊሞች ግን፤ በምርጫው ...
Read More »የመድረክ አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር፤ የተሳካ ውይይት አደረጉ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር፤ ትናንትና እሁድ መስከረም 27 ቀን የተሳካ ውይይት አደረጉ። ላለፉት 3 ሳምንታት ከሲያትል ጀምረው በአትላንታና ዴንቨር እንዲሁም ሚኒያፖሊስ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ስብሰባ ሲያደርጉ የቆዩት፤ የመድረክ ከፍተኛ አመራር አባላት፤ ፕ/ር መረራ ጉዲና፤ አቶ ስዬ አብርሀ፤ አቶ ተመስገን ዘውዴና አቶ ገብሩ አስራት በስብሰባው ላይ ተገኝተው ...
Read More »አቶ ከፍያለው አዘዘ እንደወጡ የቀሩት፤ ለስራ ወደ ዱባይ ከተላኩ በኃላ መሆኑን ሪፖርተር ዘገበ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩትና፤ ስርአቱን ከድተው አሜሪካ የገቡት አቶ ከፍያለው አዘዘ እንደወጡ የቀሩት፤ ለስራ ወደ ዱባይ ከተላኩ በኃላ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ ከፍያለው አዘዘ ወደ አሜሪካ መኮብለላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በመረዳቱም መኪናቸውን መረከቡንና፤ ስለ አቶ ከፍያለው መረጃ አልሰጠህም የተባለው ሹፌራቸውም ያለስራ እንዲቀመጥ መደረጉን ከሪፖርተር ዘገባ መረዳት ተችሏል። የአዲስ አበባ መገናኛ ...
Read More »አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባፉለት 21 አመታት ከድህነት ወለል በታች የነበረውን ህዝብ ከ38.7 ወደ 29.6 በመቶ መቀነስ ችለናል ሲሉ ተናገሩ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጨረሻም፤ የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባፉለት 21 አመታት ከድህነት ወለል በታች የነበረውን ህዝብ ከ38.7 ወደ 29.6 በመቶ መቀነስ ችለናል ሲሉ ተናገሩ። ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዛሬ ለተወካዮችና ለፌደሬሽን ምክርቤቶች አባላት በጋራ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ መንግስት አመታዊ በጀቱን ለመሸፈንና ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም፤ በብድርና በእርዳታ ገንዘብ ሲረዳ መቆየቱን ገልጸዋል። በተጻራሪው ከድህነት ወለል በታች የሚኖረው ...
Read More »የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት እንደሚያነሳ ታወቀ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሐሙስ ማምሻውን የተጠናቀቀው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ጁነዲን ሳዶ በመገምገም ከፓርቲ ኃላፊነታቸው እንዲነሱና ያለመከሰሰ መብታቸው እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሰረት በቀጣዩ ሳምንት የዓመቱን ሥራውን የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት ያለመከሰሰ መብታቸውን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ጁነዲን ከሳዑዲ ኤምባሲ ጋር ...
Read More »የኢህአዴግ ደጋፊዎች በእስራኤል አገር የሚገኙ አትዮጵያውያን ያካሄዱትን ስብሰባ ለማወክ ቢሞክሩም አልተሰካላቸውም ሲሉ አዘጋጆች ገለጡ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስራኤል አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ለመነጋገር፣ በእስራኤል አገር ስላለው የስደተኞች መብቶች ለመነጋጋር እንዲሁም በመገለላቸውና በዘረኝነት የተነሳ የመገለልና የባይተዋርነት ስሜት የሚሰማቸውን ቤተ እስራኤላውያንን ለመርዳት የተቋቋመው ማህበር ባለፈው አርብ ፣ እኤአ ኦክቶበር 5፣ 2012 በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ያደረገውን ስብሰባን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ለማሰናከል ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው በመቅረቱ በፖሊስ ተገደው ...
Read More »በጅቡቲ ለአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘናቸውን አልገለጹም የተባሉ ከ20 በላይ ኢትዮጵያውን ታፍነው ተወሰዱ
መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የታሰሩት የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ወቅት ደስታችሁን ገልጻችሁዋል ተብለው ነው። 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ እና በኢትዮጵያውያን የደህንነት ሰዎች ታፍነው በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ በደወሌ በኩል አድርገው ተወስደዋል። ከታሰሩት ወጣቶች መካከል ማሙሸት አንዳርጌ፣ ሰለሞን፣ ብዙአየሁ፣ ያሬድ በልበላ፣ አለማየሁ፣ ወንዶሰን፣ አንዳርጌ፣ ቴዎድሮስ፣ እንዲሁም ስማቸው ያለተገለጠ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል። ...
Read More »